Search This Blog

Dec 23, 2020

ይግባኝ! ይግባኝ! አሁንም ይግባኝ!

ይግባኝ! ይግባኝ! አሁንም ይግባኝ!

ከሳሽ ሆነው የቀረቡት ሴት በዕድሜ ጠና ያሉ ናቸው፡፡ ታዲያ በችሎት አንዴ መናገር ከጀመሩ የሚያስቆማቸው የለም፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለእሳቸው እንዲሰጥ ችሎት በቀረቡ ቁጥር መወትወት ስራቸው ነው፡፡ ዳኛው ዕድሜያቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት በጀመሩ ቁጥር በቀስታ ለማረጋጋት ይሞክራሉ፡፡ በመጨረሻ መዝገቡ ለውሳኔ ተቀጥሮ ቀጠሮው ሲደርስ ውሳኔው ተነበበና የእኚህ ከሳሽ ክስ ውድቅ ተደረገ፡፡
ከሳሽ እስከ መጨረሻዋ ዐረፍተ ነገር ድረስ በዝምታ እያዳመጡ ነበር፡፡ ዳኛው “መዝገቡ ስለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ” ብለው መዝገቡን ሲከድኑ በፍጹም ያልተዋጠላቸው ከሳሽ ወደ ዋናው ፍሬ ነገርና አቤቱታ ተመልሰው እጃቸውን እያወራጩ እንደገና እንደ አዲስ ክርክር ጀመሩ፡፡ ውሳኔውን የሰጡት ዳኛ ከሳሽን ለማረጋጋት ቢሞክሩም አልሆነም፡፡ ይሄኔ የዳኛው ትዕግስት አልቆ ኖሮ “ይበቃል እንግዲህ! እማማ! ከዚህ በኋላ በዚህ ፍርድ ቤት የሚቀየር ነገር የለም፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር ከተሰኙ ይግባኝ ማለት ይችላሉ” ሲሉ ቁርጣቸውን ይነግሯቸዋል፡፡
በዚህ ጊዜ ከሳሽ ውሳኔው ወዲያውኑ የሚቀየርበት ቀዳዳ የተገኘ መስሏቸው እዛው በቆሙበት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ይግባኝ! ይግባኝ! ይግባኝ ብያለሁ ይግባኝ!” ሲሉ ዳኛው ሳቃቸውን ጨርሰው ስለይግባኝ ስርዓት ካስረዷቸው በኋላ አረጋግተው ሸኝተዋቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

Popular Posts

DOCUMENTS

Criminal Procedure Code 6/2013 PDF by ሕግ እና ፍትህ on Scribd

Files

የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ 2/ 2006 PDF-Revised Federal Supereme Court s No 2/2006 by ሕግ እና ፍትህ on Scribd