፩. ጋብቻ በአንድ የክብር መዝገብ ሹም ፊት ሊፈጸም ይችላል፡።
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተጠቀሰው ቢኖርም፤ ጋብቻ በተጋቢዎቹ ሃይማኖት ወይም ባህል መሠረት ሊፈፀም ይችላል፡፡
አንቀጽ ፪ በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ
ጋብቻ በክብር መዝገብ ሹም ፊት ተፈፀመ የሚባለው አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት ጋብቻ ለመፈፀም ተስማምተው በክብር መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ ፈቃዳቸውን ሲገልጹና የክብር መዝገብ ሹሙም ይህንኑ ፈቃዳቸውን ሲቀበል ነው፡፡
ጋብቻ በሃይማኖት ሥርዐት መሠረት ተፈጸመ የሚባለው፤ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በሃይማኖታቸው ወይም ከሁለቱ በአንዳቸው ሃይማኖት መሠረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዓት ሲፈጽሙ ነው፡፡
አንቀጽ ፬ በባህል ሥርዓት መሠረት የሚፈፀም ጋብቻ
ጋብቻ በባህል ሥርዓት መሠረት ተፈፀመ የሚባለው፤ አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በሚኖሩበት አካባቢ ባህል ወይም በሁለቱ ተጋቢዎች ወይም ከሁለቱ ተጋቢዎች በአንዳቸው ባህል መሠረት የሚፀና ጋብቻ ለማቋቋም የሚያስፈልገውን ሥርዓት ሲፈጽሙ ነው፡፡
አንቀጽ ፭ ከኢትዮጵያ ውጭ ስለሚፈፀም ጋብቻ
በተፈፀመበት አገር የጋብቻ አፈፃፀም ሕግ መሠረት ከኢትዮጵያ ውጭ የተፈፀመ ጋብቻ የሕዝብን ሞራል እስካልተቃረነ ድረስ በዚህ ሕግ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
የሚፀና ጋብቻ ተፈፀመ የሚባለው ተጋቢዎቹ ለመጋባት ነፃና ሙሉ ፈቃዳቸውን ሲሰጡ ብቻ ነው፡፡
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም፤ ከባድ ምክንያት ሲያጋጥም ተጋቢዎቹ ወይም ከተጋቢዎቹ የአንዳቸው ወላጆች ወይም አሳዳሪ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት የፍትሕ ሚኒስትሩ ከመደበኛው የጋብቻ ዕድሜ ከሁለት ዓመት ያልበለጠ ጊዜ በመቀነስ እንዲጋቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
፩. በቀጥታ የሥጋ ዘመዳሞች (በወላጆችና በተወላጆች) መካከል ጋብቻ መፈፀም ክልክል
፪. ወደ ጎን በሚቆጠር የሥጋ ዝምድና፣ አንድ ወንድ ከእህቱ ወይም ከአክስቱ እንዲሁም አንዲት ሴት ከወንድሟ ወይም ከአጎቷ ጋር ጋብቻ መፈፀም የተከለከለ ነው፡፡
፩. በቀጥታ የጋብቻ ዘመዳሞች መካከል ጋብቻ መፈጸም ክልክል ነው፡፣
፪. ወደ ጎን በሚቆጠር የጋብቻ ዝምድና፣ ባል ከሚስቱ እህት ወይም ሚስት ከባሏ ወንድም ጋር ጋብቻ መፈፀም ክልክል ነው፡፡
የአንድ ሰው ተወላጅነት በሕግ መሠረት ያልተረጋገጠ ቢሆንም እንኳን በማኅበረሰቡ ዘንድ በተወላጅነት የሚታወቅ ከሆነ በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፰ እና ፱ እንደተመለከተው ጋብቻን ለማስከልከል በቂ ነው፡፡
ማንኛውም ሰው አስቀድሞ በጋብቻ የተሳሰረ ከሆነ፣ ይኸው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ ሌላ ጋብቻ መፈፀም አይችልም፡፡
አንቀጽ ፲፪ ጋብቻን በእንደራሴ መፈጸም የማይቻል ስለመሆኑ
፩. ጋብቻ ሲፈፀም ሁለቱም ተጋቢዎች ጋብቻውን በሚፈፀምበት ጊዜ በግንባር ተገኝተው ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው፡፡
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም፣ ከባድ ምክንያት መኖሩን እና በእንደራሴ አማካይነት ጋብቻውን ለመፈፀም የሚፈልገው ተጋቢ ፈቃዱን በማያሻማ ሁኔታ የገለፀ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትሩ ሲያረጋግጥ ጋብቻው በእንደራሴ ሊፈፀም ይችላል፡፡
፩. በስህተት በተገኘ ፈቃድ ምክንያት የተፈፀመ ጋብቻ አይፀናም፡፡
፪. በስህተት ምክንያት ፈቃድ ተጓደለ የሚባለው ስህተቱ መሠረታዊ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
፫. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፪) የተገለፀው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ መሠረታዊ ስህተት እንዳለ ይቆጠራል፤
ሀ) በሚያገባው ሰው ማንነት ላይ በመሳሳቱ ምክንያት አገባዋለሁ ብሎ ያላሰበውን ሰው ያገባ ሲሆን፤
ለ) የሚያገባው ሰው ሊድን የማይችል ከባድ በሽታ ወይም ለተወላጆች ሊተላለፍ የሚችል ነዋሪ በሽታ ያለበት መሆኑን ሳያውቅ ያገባው ሲሆን፤
ሐ) ሌላው ተጋቢ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም የማይችል መሆኑን ባለማወቁ ምክንያት ያገባው ሲሆን፤
መ) ሌላው ተጋቢ ከተመሳሳይ ጾታ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት የመፈጸም ልማድ ያለው መሆኑን ባለማወቅ ምክንያት ያገባው ሲሆን፡፡
፩. በኃይል ሥራ በተገኘ ፈቃድ ምክንያት የተፈፀመ ጋብቻ አይፀናም፡፣
፪. ፈቃድ በኃይል የተገኘ ነው የሚባለው፣ ፈቃዱን የሰጠው ተጋቢ ራሱን ወይም ከወላጆቹ ወይም ከተወላጆቹ አንዱን ወይም ሌላ ለእርሱ የቅርብ ዘመድ የሆነን ሰው ሊፈፀምበት ከተቃረበ ከባድ አደጋ ለማዳን ሲል ፈቃዱን የሰጠ ሲሆን ነው፡፡
፩. በፍርድ የተከለከለ ማንኛውም ሰው፣ ፍርድ ቤት ካልፈቀደለት በስተቀር ጋብቻ መፈፀም አይችልም፡፡
፪. ስለዚህ ጉዳይ ለፍርድ ቤት የሚቀርበውን ጥያቄ የተከለከለው ሰው ራሱ ወይም አሳዳሪው ሊያቀርበው ይችላል፡፡
አንቀጽ ፲፮ በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ
፩. አንዲት ሴት አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ መቶ ሰማንያ ቀን ካላለፈ በስተቀር እንደገና ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻ መፈጸም አትችልም፡፡
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም፣ ሴቲቱ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረ በኋላ አንድ መቶ ሰማንያ ቀን ሳይሞላ
ሀ) የወለደች እንደሆነ፣ ወይም
ለ) ጋብቻ የምትፈጽመው ከቀድሞ ባሏ ጋር የሆነ እንደሆነ፣ ወይ
ሐ) እርጉዝ አለመሆኗ በሕክምና የተረጋገጠ እንደሆነ፣ ወይም
መ) በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነውን ጊዜ እንዳትጠብቅ ፍርድ ቤት የወሰነ እንደሆነ በብቸኝነት ለመኖር ስለተወሰነው ጊዜ የተደነገገው ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
